ፓናማ ከተማ

ፓናማ ከተማ (እስፓንኛCiudad de Panamá /ሲዩዳድ ዴ ፓናማ/) የፓናማ ዋና ከተማ ነው።

የሚኖርበት የህዝብ ቁጥር 1,053,500 (ዙሪያ) እና 437,200 (ከተማው) ሆኖ ይገመታል። ከተማው 08°58′ ሰሜን ኬክሮስ እና 79°32′ ምዕራብ ኬንትሮስ ላይ ተቀምጦ ይገኛል።

ከተማው መጀመርያ በስፓንያውያን1511 ዓ.ም. ተመሠረተ። በ1663 ዓ.ም. እንግሊዛዊ ዠብደኛ ሄንሪ ሞርጋን ቢያጠፋውም፣ በ1665 ዓ.ም. ቅርብ በሆነበት ሰፈር ዳግመኛ ተሠራ።