ፓይታጎረስ እርጉጥ

ፓይታጎረስ እርጉጥ የምንለው ታላቁ ፈላስፋ ፓይታጎረስ (Pythagores) የፃፋቸው 3ቱ ህጎች ናቸው። ህጎቹ የሚሰሩት በ90 ዲግሪ ጎነ-ሶስቶች ላይ ነው።

1.የነው አይደለም ህግ ይህ ህግ ጎነ-ሶስቱ 90 ዲግሪ ነው ወይስ አይደለም የሚለውን የምናረጋግጥበት ነው።

 ምሳሌ:- አንድ ጎነ ሶስት  እና  የሚባሉ ነጥቦች ቢኖሩትና
     ሀለ = 9ሳ.ሜ
     ለመ = 12ሳ.ሜ
     ሀመ = 15ሳ.ሜ

(15x15)=(9x9)+(12x12)

    225=81+144
    225=225

2.የፓይታጎረስ ስሉስ ማለት የ3 ቁጥሮች ስብስብ ነው። ለማንኛውም ሙሉ ቁጥር ነ ቁጥሮቹ 2xነ፣(ነxነ)-1፣(ነxነ)+1

 ምሳሌ:- 5 ቢሆን 10፣24፣26

3.ያልተገለፀ ልኬት የርዝመስመርን ርዝመት ለማወቅ ነው።

 ምሳሌ:-የአንድ ቀጤ ጎነ 3 እግሮች 8 ሳ.ሜ. እና 15 ሳ.ሜ. ቢረዝሙ ርዝመስመሩ ስንት ነው።

(ርxር)=(8x8)+(15x15)

     =64+225
     =289
     =ራዲካል289
     =17