ፕሩሲያ

ጥንታዊ ፕሩሲያ, 1200 ዓም ግድም
ፕሩሲያ ክፍላገር በግዛቱ ጫፍ - 1863-1910 ዓም

ፕሩሲያ1517 እስከ 1939 ዓም ድረስ የጀርመን ድሮ ክፍላገር ነበር።

ከዚያ በፊት ጥንታዊ ፕሩሲያ ከ500 ዓም ያህል (በትውፊት ዘንድ) ጀምሮ እስከ 1216 ዓም ድረስ የተገኘ አረመኔ አገር ሆኖ ነበር። ቋንቋቸው ጥንታዊ ፕሩስኛባልቲክ ቋንቋዎች አባል ነበር። ከ1216 እስከ 1275 ዓም ያህል ድረስ፣ ቴውቶኒክ ሥርዓት የተባለው የመስቀለኞች ሥራዊት በጦርነት አሸነፋቸው፣ በክርስትና እንዲጠመቁ አስገደዳቸውና መሬታቸውን ያዙ። አገሩ እስከ 1517 ዓም ድረስ ቴውቶኒክ ግዛት ተባለ።

በ1517 ዓም በፕሮቴስታንት ተሃድሶ ንቅናቄ ዘመን፣ የቴውቶኒክ ግዛት አለቃ አልቤርት ዘፕሩሲያፕሮቴስታንት ሉተራን ቤተ ክርስቲያን ምዕመን ሆነና ከሮሜ ፓፓ ነጻነት ስለ አዋጀ፣ ግዛቱ ያንጊዜ የፕሩሲያ መስፍንነት ተባለ። ይህ በ«ቅዱስ ሮማዊ መንግሥት» (ጀርመን) ውስጥ ክፍላገር ነበረ። ፕሮቴስታንቶች ከብዙ አገራት በስደት ወደ ፕሩሲያ ፈለሱ፤ የክፍላገሩም ዋና ቋንቋ ጀርመንኛ ነበር። ጥንታዊ ፕሩስኛ ቀስ በቀስ እየጠፋ ከ1700 ዓም በኋላ በሙሉ ተረሳ።

የፕሩሲያ ጀርመናዊ አለቆች ደግሞ ግዛታቸውን በጀርመን ውስጥ እጅግ ለማስፋፋት ስለ ቻሉ፣ ከ«ቅዱስ ሮማዊ መንግሥት» ዘመን ቀጥሎ ጀርመን እንደ ዘመናዊ መንግሥት በማዋኸድ አንጋፋ ሚና ያለው ክፍላገር ሆነ።

ናዚ ጀርመን አዶልፍ ሂትለር1925 ዓም ወደ ሥላን ሲመጣ የክፍላገሩን ነጻ መንግሥት አጠፋ፤ ሆኖም በይፋ እንደ ክፍላገር እስከ 1939 ዓም ቆየ፤ በ1939 ዓም በጦር ጓደኞቹ አዋጅ ፕሩሲያ በይፋ ተጨረሰ።