ፕሬስቢቴሪያኒስም

የፕሬስቢቴሪያኢስም ሃይማኖት መስራች ጆን ኖክስ

'ፕሬስቢቴሪያኒስምፕሮቴስታንት እንቅስቃሴ ውስጥ በ1552 ዓም በስኮትላንድጆን ኖክስ የተመሠረተ እንደ ክርስትና የመሠለ ሃይማኖት ነው።

ሃይማኖቱ ቄሳውንት ባይኖሩት፣ የሃይማኖቱ ሽማግሎች «ፕሬስቢተር» (ሰባኪዎች) በመባላቸው ሃይማኖቱ «ፕሬስቢተርሪያኒም» የሚባለው ነው።

በ1552 ዓም በወጣው «የስኮታውያን ምስሓ» በተባለው ሰነድ የስኮትላንድ ቤተ ክርስቲያን እምነት በስኮትኛ ቀበሌኛ ተገለጸ። ለምሳሌም፦

The perfectioun of the Law and imperfectioun of man (የሕግ ፍጹምነትና የሰው ልጅ አለመፈጸም)

"THE Law of God we confess and acknawlege maist Just maist equall maist haly and maist perfyte commanding thir thingis quhilk being wrocht in perfectioun wer habill to gif lyfe and habill to bring man to eternall felicitie Bot our nature is sa corrupt sa waik and sa vnperfyte that we are neuer habill to fulfill the warkis of the law in perfectioun Yea gif we say we haue na syne euin efter we ar regenerat we dissaif our selfis and the veritie of god is not in ws And thairfoir it behuifit vs to apprehend Christ Jesus with his Justice and satisfactioun quha is the end and accomplischement of the law to all that beleve be quhome we ar set at this libertie that the curss and maledictioun of god fall not vpon ws albeit we fulfill not the same in all poinctis ffor God the father behalding ws in the body of his sone Christ Jesus acceptis oure imperfyte obedience as it wer perfyte and coueris our warkis quhilk ar defylit with mony spottis with the Justice of his sone We do not mene that we are so set at libertie that we aw na obedience to the law (for that befoir we haue plainly confessit) But this we affirme that na man in eird (Christ Jesus onlie except) hes geuin geuis or sall giue in work that obedience to the law quhilk the law requyreth Bot quhan we haue done all thingis we man fall downe and vnfenyeitlie confess that we ar vnprofitabil seruandis And thairfoir quhasaeuer bostis thame selfis of the meritis of thair awin warkis or put thair traist in the warkis of supererogatioun boist them selfis of that quhilk is nocht and put thair traist in dampnabill Idolatrie"
«የእግዚአብሔር ሕግ ከሁሉ ሐቀኛ፣ ከሁሉ ትክክለኛ፣ ከሁሉ ቅዱሰና ከሁሉ ፍጹም እንደ ሆነ፣ በፍጹምነት ተሠርተው ሕይወት ለመስጠት የቻሉ፣ ሰዎችንም ወደ ዘላለም ፍሥሓ ለማምጣት የቻሉትን ነገሮች እንዳዘዘ፣ እናመናለን፤ ነገር ግን ጸባያችን እንዲህ ብልሹ፣ እንዲህ ድካም፣ እንዲህ ያልተፈጸመ ሲሆን፣ እኛ መቸም የሕጉን ሥራዎች በፍጹምነት መፈጽም አንችልም። አዎ፣ እኛ ያለ ኃጢአት እንኖራለን ብንል ኖሮ፣ ከታደሠን በኋላ ስንኳ አንድንም ነበርና የአምላካችን እውነት በውስጣችን አይገኝም ነበር። ስለዚህም ኢየሱስ ክርስቶስን ከነፍትሑ እና ከነመጥገቡ ለመያዝ ይጠቅመናል፣ እሱም ለሚያምኑበት ሁሉ የሕጉ መጨረሻና ፍጻሜ ነውና በርሱም ምክንያት የአምላክ ርጉማንና ኲናኔ እንዳይወድቅብን በዚሁ አርነት ተቀምጠናል፤ ለእግዚአብሐር አብ በነጥቦች ሁሉ ባናከብርም፣ በወልዱ ኢየሱስ ክርስቶስ ሰውነት ውስጥ አይቶን ብልሹ መታዘዛችን እንደ ፍጹምነት ይቀብለናል፣ በወልዱም ፍትሕ በኩል በብዙ እድፎች የረከሱት ሥራዎቻችንን ይከድናልና። ለሕግ መታዘዝ ምንም ግዴታ እስከማይኖረን ድረስ በአርነት ተገኝተናል ማለታችን አይደለም (ያን ቀድሞ በግልጽ አስረድተናልና)። ነገር ግን ይህን እናረጋግጣለን፦ ማንም ሰው በምድር ላይ (ከክርስቶስ ኢየሱስ በቀር ብቻ) ሕጉ ያስፈልገውን የሕግ መታዘዝ በሥራ አልሠራም ወይም አይሠራም። ነገር ግን ሁሉንም ነገር አድርገን ሲሆን ልንደፋና የማንረባ አገልጋዮች መሆናችን ያለ ግብዝነት ልናመን አለብን። ስለዚህም በራሱ ሥራዎች ምግባር ራሱን የሚመካ ወይም በትሩፋት ሥራዎች ላይ እምነቱን የሚያድርግ ሁሉ፣ በማይሆን ነገር ይመካል፤ በተኮነነ ጣኦት ላይ እምነቱን ያደርጋል።  »

ይህ «የስኮትላንድ ምስሓ» እስከ 1641 ዓም ቆየ፣ በዚያም ጊዜ በእንግላንድ የተካሄደው ዌስትሚንስተር ጉባኤ «የዌስትሚንስተር እምነት ምስሓ» አወጣ። ይህ የዌስትሚንስተር ምስሓ በስኮትላንድ ቤተ ክርስቲያን ይፋዊ ሆነ።

: