ሬዩንዮን

ሬዩንዮን

ሬዩንዮንሕንድ ውቅያኖስ የተገኘ የፈረንሳይ ቅኝ (ጥገኛ) አገር ደሴት ነው። 802,000 ያሕል ሰዎች ይኖሩበታል።

ደሴቱ ለአረብ መርከበኞች «አድና አል ማግሪባይን» በመባል ይታወቅ ነበር። ፖርቱጊዝ1627 አ.ም. ያለ ምንም ኗሪ አገኝተውት «ሳንታ አፖሎኒያ» አሉት። ፈረንሳይ1634 ዓ.ም. ያዙትና በ1641 ዓ.ም. «ኢል ቦርቦን» አሉት። በ1785 ዓ.ም. ስሙ «ሬዩንዮን» ሆነ። ከ1793 ዓ.ም. እስከ 1802 ዓ.ም. ድረስ ግን ስሙ «ኢል ቦናፓርት» ከዚያም እስከ 1840 ዓ.ም. ድረስ እንደገና «ቦርቦን» ይባል ነበር። ከ1840 ዓ.ም. እስካሁን «ሬዩንዮን» ተብሏል።