የከተማ አርማ | |
---|---|
![]() |
ካቶቪጸ (Katowice) (ድምጽ: [ካቶቪጸ]፣ ደግሞ በጀርመንኛ "ካቶቭትዝ" Kattowitz ይባላል) የፖሎኝ ከተማ ነው። ሲሌሲያ በሚባል ታሪካዊ አካባቢ በአገሪቱ ደቡብ በክሎድኒጻ እና በራቫ ወንዞች መካከል ይገኛል። 315,123 ያሕል ሰዎች ይኖሩበታል። የከተማው ከንቲባ ፕዮትር ኡሦክ ናቸው።
የከደል ማዕድንና የብረታብረት ሥራ መኻል ነው። ዘመናዊ እና የቆዩ ሕንጻዎችና አንድ ትንሽ የአውሮፕላን ማረፊያ አለው።
የከተማነት ሁኔታ በሕግ የተቀበለው በ1857 ዓ.ም. ነበር። ሲሌሲያ ለረጅም ጊዜ የጀርመን ክፍላገር ሆኖ ከተማው እስከ 1910 ድረስ በጀርመን ውስጥ ይገዛ ነበር።
ከ1946 ዓ.ም. እስከ 1948 ድረስ የካቶቪጸ ስያሜ "ስታሊኖግሮድ" ማለት "የስታሊን ከተማ" ነበር። ይህ ስም የተሰጠው በኮሙኒስቶች ወገን ነው።
I. ከተማ
II. ስሜን መንደር
III. ምዕራብ መንደር
|
IV. ምሥራቅ መንደር
V. ደቡብ መንደር
|