ይህ መጣጥፍ የውክፔዲያ የአቀማመጥ ልምዶችን እንዲከተል መስተካከል ይፈልጋል። |
ፀጋዬ ገብረመድኅን (1928-1998) ቦባዳ ተብላ በምትታውቅ አምቦ ካተማ አካባቢ በምትገኝ ተራራማ ቦታ ተወለዱ። በአምቦ ማአረገ ሕይወት ቀ.ኃ.ሥ. ትምህርት ቤት ከዚያም ጀነራል ዊንጌትና በአዲስ አበባ የንግድ ትምህርት ቤት በአገር ውስጥ ትምህርታችውን ከገፉ በኋላ በቺካጎ ብላክስቶን በህግ ትምህርት ተመርቀው በ1952 እንደ ወጡ በለንደን ከተማ የቴአትር ትምህርት በሮያል ኮርት ቴአትርና በፓሪስ ኮሜዲ ፍራንሴዝ ተከታትለዋል። ከ1954 እስከ 1964 የብሔራዊ ቴአትር በአርቲስቲክ ዳይሬክተርነት አገለግለዋል። ከዚያም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቴአትር ዲፓርትመንትን አቋቁመዋል።
ሆኖም በ1960ዎቹ ደርግ አብዛኛውን የቴአትር ሥራዎቻቸውን ሲያግድ እሳቸውንም ለማሰር በቅቷል።
ብላቴን ሎሬት ጸጋዬ በርካታ ግጥሞችን፥ የቴአትር ሥራዎችን የተለያዩ መጣጥፎችንና ዘፈኖችን አበርክታዋል። ጸጋዬ በ1990 ለጉበት በሽታ ሕክምና በመሻት ወደ ማንሃታን በሄዱበት አርፈዋል። በአዲስ አበባ በቅድስት ሥላሴ ቤተክርቲያን ተቀብረዋል። ነፍሳቸውን በአብርሃም እቅፍ ያኑርልን::
እንደ፡ አዉሮፓ፡ አቈጣጠር፡ በ 2002 ዓ.ም. የብላቴን ሎሬት ጸጋዬ፡ ገብረ መድህን፡ ግጥም፡ ("Proud to be African") አዲስ፡ በተመሰረተው፡ የአፍሪካ፡ ኣንድነት፡ ማሕበር፡ በሕዝብ፥ መዝሙርነት፡ ተመርጧል።
ከሳቸዉ፡ ጽሁፎች፡ መካከል፡ የሚከተሉት፡ ዪገኛሉ ። ... .....
ዝክረ ፀጋዬ

ብላቴን ጌታ ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድሕን እነሆ በሞት ከተለየን ድፍን አራት አመታት ተቆጠሩ። ትዝታም አራተኛ ሙት አመቱን (February 25, 2006) በማሰብ ስራዎቹን በግርድፉም ቢሆን በማውሳት እነሆ የፀጋዬ ዝክር ትላለች።

የእረፍት ዋዜማ፦
ፀጋዬ ከማረፉ አራት አመታት ቀደም ብሎም በዶ/ር ኄራን ሠረቀብርሃን አማካይነት በዋሽንግተን ዲሲ የፀጋዬ ግጥሞች በሲዲ ተቀርፀው ተመርቀዋል። 1 የስንብት ዝግጅት ይሆን። ትንቢት አስቀድሞ ለነገር እንዲሉ።

ፀጋዬ ከማረፉ አስራ አምስት ቀን አስቀድሞ የ«አንድምታ» ባልደረባ አናግሮት ነበር። እስኪ ሁለቱን የሎሬት ፀጋዬን ጥኡም ወጎች ላስቀድም።<
በአፄ ምኒልክ ዘመን እንግሊዞች ቱርካና ሃይቅ አካባቢ ዝሆን ያድኑ ነበርና አንዴ አደናቸውን ተከትለው ሲገስግሱ ከኢትዮጵያ ኬላ ደርሰው ኖሮ ድንበር አላሳልፍ ካሉ የኬላ ጠባቂዎች ጋር የተኩስ ልውውጥ ይደረግና ከአዳኞቹ አንዱ በዚሁ ምክንያት ይሞታል። እንግሊዞችም አቤቱታ ያሰሙና ነገሩ አባ መላ (ፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ) ዘንድ ይደርሳል። እንግሊዞቹ ያለአግባብ ሰው እንደተገደለባቸው አመልክተው የደም ካሳ እንዲሆናቸው ከኢትዮጵያ ድንበር ውስጥ መሬት እንዲሰጣቸው ነበር የጠየቁት። አባመላ ነገሩን ያጠኑና ችግር እንደሌለው ለእንግሊዞቹ ይገልጻሉ። ነገሩ ከመፈጸሙ በፊት ግን “ይኸ ህግ እናንተ ሃገርም እንደሚሰራበት ማየት ስለምንሻ በሰነድ መልክ ረቂቁ ካለ እስቲ እንየው። እውነት የእንግሊዝ ሰው የዌልስን ሰው ቢገድል እንግሊዝ ከመሬቷ ለዌልስ የምትሰጥ ከሆነ እኛም እንሰጣለን። እሱም የሚሆነው ለተገደለብን የኬላ ጠባቂ ካሳ የሚሆን ከቱርካና ሃይቅ አካባቢ መሬት ከተረከብን ይሆናል ብለው መለሷቸው።<
ሌላው ደግሞ የሎሬት ፀጋዬ ከ«ሕይወት ቢራቢሮ» መታተም ጋራ ተያይዞ ለአንድምታ ባልደረባ ያወጋው ነው። መጀመሪያ የግጥሟን ቅንጫቢ ነቢይ መኮንን ከተረካው እነሆ!]]
«...ምን አይተሻል ከቄጤማ፣ ምን አይተሻል ከለምለሙ< ቀን አብረሽ አብበሽ ውለሽ፣ ሲመሽ አብረሽ መስለምለሙ?...< አስተምሪኝ ቢራ ቢሮ፣ ሰው ለመባል አለኝታዬ< ቀድሞ የት ነው መነሻዬ< ሲመሽ የት ነው መድረሻዬ...< ሲተረትማ ሲወጋ፣ ከየብልጭታው ውጋጋን< የሰው አራዊት የአእዋፍ፣ ውስብስብ ነገደ-ጉንዳን< ሲነሳ ሲሮጥ ሲደፋ፣ ሲያጋድል ሲያዛባ ሚዛን< በማይመጠን ታላቅ ኃይል፣ በተፈጥሮ ግዙፍ ሥልጣን< ሊፍተለተል ይወለዳል፣ ሳይነቃ ይወድማል ይባላል
ልደቱ ዕድሜና ሞቱ፣ አለማቋረጥ ይጓዛል፤
ይኸ ይሆን አልፋ - ኦሜጋ? ይኸ ይሆን አስቀድሞ ቃል?» < ፀጋዬ እንዲህ አለ። «እሷ ግጥም በጋዜጣ ታትማ በወጣች ማግስት መንግስቱ ለማ ከቢሮዬ መጥቶ ቢራውን እስቲ አምጣው ወይስ ዝም ብለህ ነው ቢራ ቢሮ ያልከው» ብሎ እንደቀለደብኝ ትዝ ይለኛል።ትንሽ ትከዝ ብሎም «መንግስቱ ምን የመሰለ ደማም ቋንቋ የነበረው ሰው ነበር።አሁን እኮ ደማም ቋንቋ የሚናገር ሰው ሁሉ ጠፋ»።አፈሩ ይቅለለውና ሎሬት ፀጋዬ የኛን ትውልድ <<ጫት አመንዣኪ>> ትውልድ ነበር የሚለው።እንዲህ እንደነሱ ዘመን ባይጎሉም ውድድሩም ቢጠናባቸውም አሁንም እኮ አንቱ የተባሉ ወጣት ደራሲያን ገጣሚያን አሉን። ጊዜው ሲደርስ እንዘክራቸዋለን።

አምቦ አካባቢ ልዩ ስሟ ቦዳ ከኦሮሞና ከአማራ ወገኖቹ የተወለደው ፀጋዬ ገና በልጅነቱ ነበር ሶስቱ ቋንቋዎች አማርኛ፡ እንግሊዘኛና ኦሮሞኛ የተገሩለት። በትምሕርት እየጎለመሰ ሲሄድም ደራሲነቱን ገጣሚነቱን እንዲያ ሲልም ፀሃፊ-ተውኔትነቱን በዋነኛነት በጎልማሳነት ዘመኑ ደግሞ ማህበረሰባዊ ሃያሲነት እና የአፍሪካ የሰው ዘር እና የቅብጥ ቋንቋ እና ባህል ጠቢብነትን አክሎበት እስከ እለተ ህልፈቱ ዘልቋል። በኩላሊት በሽታ መለከፉ እና አለመዳኑን እንዲያም ሲል በጉብዝናው ወራት ያላሰበውን ስደት በሕክምና ሳቢያ የአብራኩ ክፋይ ልጆቹ ወዳሉበት አሜሪካ አቅንቶ በዚያው አሸልቧል። የማሳረጊያ ግጥሙም ይህንን ተስፋ ቢስነትን አመላካች ይሆን።
የማይነጋ ሕልም ሳልም

የማይድን በሽታ ሳክም< የማያድግ ችግኝ ሳርም< የሰው ሕይወት ስከረክም< እኔ ለኔ ኖሬ አላውቅም<
መደብ:የኢትይዮጵያ ሰዎች